ዛሬ ቀኑ እጅግ በጣም ደስ ይላል!! አድርገህ የማታውቀው ነገር! ከዚህ በፊት አድርገህ የማተውቀውን ነገር ማድረግ ስትጀምር፣ ከዚህ በፊት አግኝተህ የማታውቀውን አዲስ ነገር ማግኘት ትጀምራለህ፡፡ ከዚህ በፊት ያልነበረህን ነገር ለማግኘት ከፈለክ ከዚህ በፊት አድርገህ ያማተውቀውን ነገር ለማድረግ ፈቃደኛና ተነሳሽ መሆን አለብህ፡፡ ያንንው ነገር እየደጋገምክ የተለየ ነገር መጠበቅ ሞኝነት ስለሆነ ማለት ነው፡፡ ከእነዚያው ሰዎች ጋር እየዋልክ ከእነሱ [...]